Sunday School

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤዛ ኵሉ ሰንበት ት/ቤት የተመሰረተው 1996 ዓ.ም. ሲሆን ይህ ሰ/ት/ቤት ላለፉት 29 ዓመታት ሕጻናትን ታዳጊያን እና ወጣቶችን አሰባስቦ መርሐ ግብር በመንደፍና በመዘርጋት ቃለ እግዚአብሔር ሲያስተምር የቆየ ሰ/ት/ቤት ነው።

የቤዛ ኵሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የተለያዩ የአገልግሎት ክፍላትን የያዘ ሲሆን እነዚህም ጽሕፈት ቤት ፣ ትምህርት ክፍል ፣ ግንኙነት ክፍል፣ መዝሙር ክፍል፣ ልማት ክፍል፣ ሒሳብ ክፍል፣ ሕጻናት ክፍል፣ ሚዲያ ክፍል፣ ኪነጥበብ ክፍል እና የበገና ትምህርት ክፍል በአጠቃላይ 10 ክፍላትን የያዘ ሲሆን በእነዚህ የአገልግሎት ክፍላት ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች:-ለሰንበት ት/ቤቱ አባላት ተከታታይ ኮርሶችን የሚሰጥ ሲሆን ለሕጻናት እና ለታዳጊ ወጣቶች የቃለ እግዚአብሔር የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፣ የበገና ትምህርት በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ በመስጠት ላይ ይገኛል::